የኮምቦልቻ እንሰሳት በሽታ ቅኘት፣ ጥናትና ምርመራ ላቦራቶሪ አጭር መግለጫ

የኮምቦልቻ እንሰሳት በሽታ ቅኘት፣ ጥናትና ምርመራ ላቦራቶሪ መልክአ ምድር አቀማመጥ በሰሜን 11o.084ና በምሥራቅ 0390.737 ከባህር ወለል በላይ 1830 ሜትር ሲሆን ከአዲስ አበባ በ375 ኪ.ሜ፣ ከባህርዳር 500 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የሚገኝ በምስራቅ ከአፋር፣  በሰሜን ከትግራይ፣ በምዕራብ ከሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም (አማራ ክልል)፣ ምዕራብ ሸዋ (ኦሮሚያ ክልል)ና በደቡብ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጋር ይጎራበታል፡፡

ላቦራቶሪው ከ1957 ዓ.ም ጀምሮ የተቋቋመና በአማራ ክልል ከሚገኙ ሁለት ላቦራቶሪዎች አንዱ ሆኖ በምስራቁ ክፍል ያሉትን 5 ዞኖች (ሰሜን ሽዋ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ)፣ ሦስት ሪጅዮፖሊታን ከተሞች (ኮምቦልቻ፣ ደብረብርሃንና ወልድያ)ና አንድ ሪጅዮፖሊታን (ደሴ) ያካተተ ሲሆን በስሩም 65 የገጠር ወረዳዎች16 የከተማ መስተዳድሮች ሲኖሩ በነዚህም ውስጥ1358 የገጠር ቀበሌዎችና130 የከተማ ቀበሌዎች አካቶ የሚሰራ ሲሆን የቆዳ ስፋቱም 58,971 ስር ኪሎሜትር ስፋትና 8,234,547 የህዝብ ብዛት  ይገኛል፡፡

የእንሰሳት ብዛትን በተመለከተ 5,395,789 የዳልጋ ከብት፣ 4.405.448 በግ፣ 3,217,999 ፍየል፣ 1,256,649 ጋማ ከብት፣ 79,584 ግመል፣ 5,029,624 ዶሮዎች፣ 334,085 የንብ ቀፎ የሚረቡ ሲሆን

 ላቦራቶሪው በእንሰሳት በሽታ ዙሪያ ቅኝት፣ ጥናትና ምርመራ እያደረገ የአካባቢውን እንሰሳት አርቢ ማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ትልቅ ተቋም ነው፡፡  ላቦራቶሪው 15 የቴክኒክና 31 ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ቴክኒክ ክፍሉ በአራት ክፍሎች ማለትም ማይክሮ ባዮሎጅ፣ ፓራሳይቶሎጅ፣ ፓቶሎጅና ኢፒዲሞሎጅ ተዋቅሮ የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት ያከናውናል፡፡

የላቦራቶሪው ዋና ዋና ተግባራት:- 

የበሽታ ቅኝት ማካሄድ፡- ላቦራቶሪው በሥራ ክልሉ ውስጥ አዲስ ድንበር ዘለልና ተዛማች የእንስሳት በሽታ እንዳይገባ ያጠናል፣ የቁጥጥር ስትራቴጂ ያቀርባል፡፡ በዚህ ወቅት በሽታ ከተከሰተ በፍጥነት ያጣራል፣ የሥርጭት መጠኑንና ስጋትን ያጠናል፣ አዳዲስ ክስተት ያሉበትን አካባቢዎች ይከታተላል፡፡ በተጨማሪም ከክትባት ዘመቻ በላ የመድኅን ሁኔታ ይመረምራል፣ ይከታተላል የጥናቱን ውጤት ለሚመለከተው ያቀርባል፡፡

የበሽታ ጥናት ማካሄድ፡- ላቦራቶሪው በሥራ ክልሉ ውስጥ የተለያዩ የእንስሳት በሽታ ስርጭት፣ የጉዳት መጠን፣ ባህርይ ወዘተ. በጥልቀት በማጥናት ለቁጥጥር፣ ለመከላከልና ለመቀነስ ስትራቴጂ ነድፎያቀርባል፡፡ ለምሳሌ፡- የቲቢ በሽታ፣ የውርጃ በሽታ፣ የጉርብርብ በሽታ፣ የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ ወዘተ. በተጨማሪም የመድኃኒት ብቃትና የክትባት ችግር በማጥናት ሳይንሳዊ መረጃ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡

የናሙና ምርመራ ማካሄድ፡- በላቦራቶሪው የሥራ ክልል ውስጥ የተለያዩ የእንስሳት በሽታ ፍንዳታ ሪፖርት ከወረዳ ባለሙያ ሲቀርብ፣ በጥናትና በቅኝት ወቅት የተሰበሰቡ ናሙናዎችን በምርመራ ያረጋግጣል ከአቅም በላይ ሲሆን ለእንሰሳት ጤና ኢንስቲቲዩት (Animal Health Institute) ይልካል ውጤቱንም ተከታትሎ ለተጠቃሚ ከነመፍትሄው ያሳውቃል፡፡

የላቦራቶሪው ዓላማ፣

èበስራ ክልሉ የበሽታ ፍንዳታ ሲከሰት ባለሙያዎች በቦታው በመገኘትና ስለበሽታው ምንነት አስፈላጊውን ማጣራትና ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ የተከሰተው በሽታ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመቆጣጠር የሚያስችል የመፍትሄ ሃሳብ ማቅረብ፡፡

èከበሽታ ፍንዳታ፣ ከእንሰሳት እርባታ ጣቢያዎች እንዲሁም ከጥናትና ቅኝት የሚመጡ ናሙናዎችን መመርመርና ውጤቱንም በፍጥነት ለሚመለከተው አካል በማስተላለፍና መረጃውንም በተገቢው ሁኔታ በማጠናቀር ለወደፊቱ የመከላከል ስትራቴጂ መንደፍና መፈጸም፤

èበድንበር ዘለልና በእንሰሳት ምርትና ምርታማነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ በሽታዎችን ቅኝትና ጥናት በማካሄድ የመከላከልና የመቆጣጠር ስትራቴጂ በመንደፍ ለሚመለከተው አካል ማቅረብና በተግባራዊነቱም ላይ መሳተፍ፡፡

èከፌደራል የእንሰሳት በሽታ መከላከልና ቁጥጥር፣ ከእንሰሳት ጤና ኢንስቲቲዩት (Animal Health Institute)፣ ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት (National veterinary Institute)፣ ከአጎራባች ክልሎችና ዞኖች ጋር በጋራ በቅንጅትና በመተባበር መንፈስ የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ሥራን መስራት፣

èከወረዳ የሚመጡ የበሽታ ፍንዳታና የክትባት ሪፖርቶችን በማሰባሰብ፣ በማጠናቀር፣ በመተንተንና ዶክመንት በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል በወቅቱ በማሰራጨት ለበሽታ ቁጥጥርና መከላከል ዕቅድ እንዲያገለግል ማቅረብ፡፡

èአዳዲስ የጥናትና የምርመራ መሳሪያዎችና ዘዴዎች በላቦራቶሪው እንዲጀመርና እንዲስፋፋ በማድረግ ላቦራቶሪው የመመርመር አቅሙን በማሳደግ ወደ ሪፈራል ላቦራቶሪ የሚላኩትን ናሙናዎች በመቀነስና  ለተከሰቱ በሽታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት፣

èለመስክ የወረዳና የዞን ባለሙያዎች ስለ በሽታ አሰሳና ቅኝት እንዲሁም ናሙና ማሰባሰብና መመርመር የሚያስችሉ ስልጠናዎችን መስጠት ናቸው፡፡

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |