ዜና
በኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 04 በወተት ሃብት ልማት ስራ ጥሩ እንቅስቃሲ እያደረጉ ያሉ ግለሰብ
አቶ እንድሪስ አደም ነዋሪነታቸው በኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 04 ነዋሪ ሲሆኑ ግለሰቡ ከዚሀ በፊት የመንግስት ሰራተኛ የነበሩ ሲሆን ግለሰቡ ከ 2010 ዓ.ም ጀምሮ 5 የወተት ላሞችን በመያዝ ወደ ስራ የገቡ ሲሆን አሁን ላይ ጊደሮች እና ጥጃዎችን ጨምሮ ከ 30 ያላነሱ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸውን እንስሳት ይዘዋል፡፡ ግለሰቡ ለላሞቻቸው ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የሚያስችል እውቀትና እና የስራ ተነሳሽነት ያላቸው ሲሆን በባለሙያዎች ዘንድ የሚደረግላቸውን ድጋፍም በአግባቡ እንደሚተገብሩ የወተት ላም እርባታ ጣቢያቸውን በጐበኝንበት ወቅት ማረጋገጥ ችለናል፡፡
ዜና
በ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ሀርቡ 02 ቀበሌ በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት የኘሮጀክት ድጋፍ በዶሮ ሃብት ልማት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች
- አቶ ጀማል አወል ነዋሪነታቸው በቃሉ ወረዳ ሀርቡ ቀበሌ ሲሆን ግለሰቡ በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት 30 የእንቁላል ዶሮዎች፣ የመመገቢያና የመጠጫ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጎላቸው በዶሮ እርባታ ወደ ስራ የገቡ ግለሰብ ሲሆኑ ግለሰቡ ለዶሮዎች ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ በመቻላቸው በቀን 27 እንቁላል ያገኛሉ፡፡
- አቶ ጀማል የሱፍ ነዋሪነታቸው በቃሉ ወረዳ ሀርቡ ቀበሌ ሲሆን ግለሰቡ በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት 30 የእንቁላል ዶሮዎች፣ የመመገቢያና የመጠጫ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጎላቸው በዶሮ እርባታ ወደ ስራ የገቡ ግለሰብ ሲሆኑ ግለሰቡ ለዶሮዎች ተገቢውን እንክብካቤ ባለማድረጋቸው በቀን ከ 17-20 እንቁላሎችን በአማካኝ ያገኛሉ፡፡
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከብሄራዊ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል ማአከል ጋር በመተባበር ከታህሳስ 3—12/04/2013 ዓ.ም በቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት ማአከል ቁጥራቸዉ 48 ለሚሆኑ የአዳቃይ ቴክኒሻን ባለሙያዎች የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና ተሰጠ ፡፡
የአማራ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ከሚሰራቸዉ ስራዎች አንዱ የእንስሳትን ዝርያ በመረጣና በማዳቀል የማሻሻል ስራ ነዉ፡፡ በክልሉ 310 የመንግስት፣23 የግል፣21 የአርሶ አደር እንዲሁም 23 በወተት ተፋሰስ ወረዳዎች በሚገኙ የወተት ህብረት ስራ ማህበራት ያሉ አዳቃይ ቴክኒሻኖች በጥቅሉ 377 የሚሆኑ አዳቃይ ቴክኒሻኖች በተለያዩ ጊዚያት በዝርያ ማሻሻል ስራ የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ አድርጓል ፡፡ ኤጀንሲዉ የእነዚህ አዳቃይ ቴክኒሻኖችን የመፈጸም አቅም በማሳደግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ከሚሰራቸዉ በርካታ ስራዎች አንዱ የሙያተኞችን አቅም በአጫጭር ስልጠናዎች በየጊዜዉ ማሳደግ ነዉ፡፡
ዜና
የአብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከicipe Moyeshe ፕሮጀክትጋር በመተባበር ከታህሳስ 3__4/2013 በባህርዳር ከተማ የማር ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንሱ አካሄደ፡፡
የአማራ ክልል ባለው የአየር ፀባይ እና የመሬት አቀማመጥ ለተለያዩ የቀሰም እፅዋቶች እንዲኖሩ ምቹ አከባቢ በመሆኑ
ለንብ ሃብት ልማት ተግባር ተስማሚ ነው ክልላችን 1,349,320 ህብረ ንብ እንዳለውና ከሃገር አቀፍ ጥቅል የህብረ
ንብ ብዛት ደግሞ 20% ድርሻ እንዳለው የ2012 የማዕከላዊ ስታትስቲክስ /CSA/ መረጃ ያሳያል፡፡
ዜና
የደቡብ ጎንደር ዞን እንስሳት ሃብት ልማት ተ/ጽ/ቤት የ2012 በጀት ዓመት የዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2013 እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ
የደቡብ ጎንደር ዞን እንስሳት ሃብት ልማት ተ/ጽ/ቤት የዞኑ ክፍተኛ አመራሮች፤ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የድርጀት ጽ/ቤት ሃላፊዎች፤ በዞኑ እንስሳት ሃብት ልማት ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የወረዳ ተ/ጽ/ቤት ሃላፊዎችና ቡድን
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የ2013 እቅድ የስትሪንግ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡
የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የ2012 በጀት አመት የዋና ዋና ስራዎችን እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2013 ዓም እቅድ ትውውቅየስትሪንግ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በቀን 22/01/2013 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ አካሄደ፡፡
ኘሮጀክቱ በ2012 በጀት አመት በወተት ሃብት ልማት፣ በቀይ ስጋ፣ በዶሮ ሀብት ልማት እና በዓሣ ሃብት ልማት በአርሶ አደር እና በተደራጁ ወጣቶች ዙሪያ የተሰሩ የፊዚካል ስራዎችን ከፋይናንስ አፈፃፀሙ ጋር በዝርዝር በሪፖርት ያቀረበ ሲሆን የስትሪንግ ኮሚቴ አባላትም በቀረበው ሪፖርት በስፋት ከተወያዩ በኃላ የሚከተሉትን ዋና ዋና ገንቢ አስተያየቶች አስቀምጠዋል፡፡
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ለ15 ወረዳዎች የአሰልጣኞች ስልጠና አካሄደ፡፡
የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የእንስሳት አያያዝ ትግበራ ለመመዘን የሚያገለግል መመሪያ ዙሪያ በፕሮጀክቱ በታቀፉ 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የዘርፉ ሃላፊዎች ፤ሙያተኞች እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ከ14-18/01/2013 ዓ.ም በፍኖተ ሰላም ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠና አካሄደ፡፡ ስልጠናው በቀጣይ ፕሮጀክቱ በሚሰራባቸው ወረዳዎች ለሚገኙ የቀበሌ ሙያተኞች እንደሚደርስ ተጠቁሟል፡፡
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የ2012 እቅድ አፈፃፀም እና የ2013 የእቅድ በቴክኒክ ኮሚቴ ተገመገመ፡፡
የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የ2012 በጀት አመት የዋና ዋና ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና የ2013 በጀት አመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በ 3/01/2013 ዓ.ም በእንጀባራ ከተማ አካሄደ፡፡ ፕሮጀክቱ በበጀት አመቱ ያከናወናቸዉን ዋና ዋና ስራዎች ያቀረበ ሲሆን
ከወጣቶች አንጻር የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች በተመለከተ
በደሮ ለ2460 ወጣቶች(ሴ 1007) ለ1 ወጣት ባአማካኛ 25 ደሮዎችን እና የደሮ መጠላይ ግንባታ፣መኖ፣ መመገቢያና መጠጫ ቁሳቁስ የማሟላት
በቀይ ስጋ ለ1405 ወጣቶች (ሴ 348) በአማካኝ ለ15 ወጣቶች 30 በግ፣የበግ መጠለያ ፣መኖ፣መመገቢያና መጠጫ ቁሳቁስ የማሟላት
በአሳ ለ170 ወጣቶች(ሴ 25) የሸድ ግንባታ፣የመበለቻ ቁሳቁስ፣ዲፕ ፍሪጅ ፣ጄኔረተር እና የማጓጓዣ ቁሳቁሶችን የማሟላት ስራ መከናወኑ ተጠቅስዋል፡፡