ዜና
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሃይለማርያም ከፍያለው የቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽቤት ሃላፊ ዶር ጋሻው ሙጨ በቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስጀመሪያ ፕሮግራም እና የመስክ ምልከታ ላይ የሰጡት አስተያየት
ዜና
በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት የደብረ ዘይት ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዮት የእንስሳት ስነ-ተዋልዶ ከፍተኛ ተመራማሪ አቶ ታምራት ደገፋ በማዕከሉ ተገኝተው የሰጡት አስተያየት
ዜና
የቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል ሃላፊ አቶ ፈንታሁን ዳኛው በማዕከሉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አስመልክቱ የሰጡት ማብራሪያ
ዜና
የቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄደ ፡፡
የአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የሚመለከታቸው የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎች ፣ በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ፣ ከምርምር ተቋማት የመጡ የስራ ሃላፊዎች እና ተመራማሪዎች ፣እንስሳት ሃብት ልማት ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች እና የዘርፉ የዞንና የወረዳ የሚመለከታቸው አመራሮች እና ሙያተኞች በተገኙበት በ24/03/2014 ዓ.ም በቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስተዋወቅ እና ማዕከሉ ከዝርያ ማሻሻል እና መኖ ልማትና ስነ አመጋገብ ከማሻሻል አንጻር የሚሰራቸውን ስራዎች ለተሳታፊዎች የማስጎብኝት ፕሮግራም አካሄደ ፡፡
ዜና
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በእንስሳት ዘርፍ የተሰማሩ የኒዬኖችን በከፍተኛ ደረጃ ድጋፍ ለማድረግ የተዘጋጀ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በክልላችን በ15 ወረዳዎች በእንስሳት ዘርፍ በ4 እሴት ሰንሰለቶች (ወተት፣ ቀይ ስጋ፣ ዓሳ እና ዶሮ) ላይ ተመሳሳይ ምርት የሚያርቱ አ/አደሮችንና ወጣቶችን በጋራ ፍላጎት ቡድን በማደራጀት 140000 ብር፣ በደረጃ ሁለት በጋራ ፍላጎት ተደራጅተው ትርፍ ምርት በማምረት ላይ የሚገኙትን ወደ ህብረት ስራ ማህበር በማሳደግ 1.3 ሚሊዬን ብር እና በከፍተኛ ደረጃ የማቀነባበር ስራ ላይ ለተሰማሩ ዩኒየኖችና ለተሻሻሉ ማህበራት 8.5 ሚሊዬን ብር በመሰረተ ልማት፣ በቁሳቁስ፣ በግብዓትና ስልጠና ድጋፍ በማድረግ የምርትና ምርታማነት በማሳደግ ድጋፍ እያደረገ ይኛል፡፡
ዜና
ለቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት ማዕከል ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጣና ተሰጠ፡፡
የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከ29-30/01/2014 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ ለቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜትና ጥበቃ ማዕከል ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አካሄደ ፡፡ ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የኤጀንሲው ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ፈንቴ ቢሻው ሲሆኑ ኃላፊው በመክፈቻ ንግግራቸው ማዕከሉ የተሻሻሉ ዝርያዎችን እያባዙ ለአርሶ አደሩ በማሰራጨትም ሆነ ንጹህ የፎገራ ዳልጋ ከብት ዝርያዎችን ጠብቆ ከማቆት አንጻር ትልቅ ኃላፊነት የተጣለበት መሆኑን በመግለጽ ይሁን እንጅ ማዕከሉ የተጣለበትን ተግባርና ሃላፊነት በሚፈልገው መጠን አሟልቶ በመፈጸም እረገድ ውስንነቶችን ያሉ መሆኑን ሃላፊው ገልጸው ይህን ስልጠና በሰራተኞች ዘንድ የሚታየውን የክህሎት ክፍተት በመቅረፍ ለቀጣይ ስራ ውጤታማነት አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል፡፡
በስልጠናው ሰልጣኞች የዳልጋ ከብት አያያዝና እንክብካቤ በተመለከተ ከእንስሳት እርባታ እና ጤና አንጻር ሊተኮርባቸው የሚገቡ መሰረታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልቶችን በመወያየት ለቀጣይ ስራዎች አቅም የሚሆን ግንዛቤ ይይዛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የቻግኒ የዳ/ከብት ዝርያ ማሻሻል እና ብዜት ማዕከል የዝርያ ማሻሻልና ጥበቃ የቀጣይ ተግባራት አቅጣጫ በአቶ አህመድ አልቃድር.pptx
የዳ/ ከብት ጤና አጠባበቅ ዙሪያ ለቻግኒ የብዜት ማዕከል ባለመያዎች እና ተንከባካቤዎች የተዘጋጀ ስልጠና በዶ/ር ታምሩ ተሰማ.pptx
ዜና
የሆርሞን ሲንክሮናይዜሽን ቴክኖሎጂ ውጤታማ ለማድረግ የምንከተላቸው የአሰራር ሞዳሊቲዎች በተመለከተ በአቶ ደመላሽ አይችሌ የተሰጠ ስልጠና ፡፡
- ኤጀንሲው ከ 19-21/1/2014 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ ባካሄደው መድረክ የሰሜን ሽዋ፣ ምዕ/ ጐጃም እና የኦሮሞ/ብ/አ/ ዞን
- በፎገራ ወረዳ ዓሣን ከእሩዝ ማሳ ጋር አጣምሮ የመከወን የሰራ እንቅስቃሴ ተጎበኝ
- የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የ2013 በጀት ዓመት የዝርያ ማሻሻል አፈፃፀም እና የ2014 ዓ.ም የዝርያ ማሻሻል እቅድን ገመገመ፡፡
- የተሻሻለ የቤተሰብ ደሮ እርባታ የሙከራ ትግበራ የሚተገበርባቸዉ ሞዴል መንደሮች በተመለከተ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሄደ