የኤጀንሲው ዋና ስራ አስኪያጅ መልዕክት
የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በደንብ ቁጥር 81/2003 ዓ.ም በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት የተቋቋመ ሲሆን ክልላችን ለእንስሳት ሃብት ልማት ምቹ የሆነ የአየር ንብረት ያለው ከመሆኑም በተጨማሪ እንደ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ 2015/2016 ጥናት በክልላችን 15454923 ዳልጋ ከብት 9797248 በግ 6085912 ፍየል 19958894 ደሮ 3478747 የጋማ ከብት 1328235 የንብ መንጋ 63500 የግመል ሀብት ያለ ቢሆንም በህ/ሰቡ ኋላቀር የሆነ የአረባብ ዘዴ ጋር ተያይዞ በሚስተዋሉ ምርታማ ያልሆኑ ዝርያዎች ቁጥር ላይ ብቻ አተኩሮ የመስራት፣ መኖን በተገቢው መልኩ አልምቶ በአግባቡ ያለመመገብ እንዲሁም የእንስሳትን ጤና በተገቢው መልኩ ከመጠበቅ አንጻር በሚስተዋሉ ችግሮች ምክንያት ህ/ሰቡም ሆነ ሀገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ጥቅም እንዳታገኝ አድርጓት ቆይቷል፡፡
More...